Welcome

የ'አዲስ:ዜና'ን መተግበሪያ ያውርዱ

የተሻለ የንባብ ተሞክሮ ለማግኘት እና የቅርብ ጊዜ ዜናዎችን ለማየት መተግበሪያውን ያውርዱ።!

Download
Cancel
Image:AddisZena
አዲስ ዜና | Addis Zena
ለ6ኛው ዙር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ሥልጠና እየተሠጠ ነው

መስከረም 13/2014 (ዋልታ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለ6ኛው ዙር የምክር ቤት አባላት በምክር ቤቱ አሠራር ዙሪያ ሥልጠና እየሠጠ ይገኛል፡፡

ሥልጠናው በዋናነት በምክር ቤቱ አሠራሮች፣ ሥነ-ሥርዓቶች፣ ደንቦችና ጽህፈት ቤቱ በሚሠጠው አገልግሎት ዙሪያ ማስተዋወቅ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው ተብሏል፡፡

በስልጠናውም ምርጫ ካልተደረገባቸው አካባቢዎች በስተቀር በሀገሪቱ በሚገኙ የምርጫ ክልሎች ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአባልነት የተመረጡ ሁሉ ተሣታፊ ሆነዋል፡፡

ስልጠናው አባላቱ በምክር ቤቱ አሠራርና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ታሣቢ ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

6ኛው ዙር የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መስከረም 24/2014 ዓ.ም የመንግስት ምስረታ እንደሚያደርግ ይታወቃል፡፡

logoWalta rc43 cc0
አሁን የናኙ
Copyright © All rights reserved | Marvellous LLC