Welcome

የ'አዲስ:ዜና'ን መተግበሪያ ያውርዱ

የተሻለ የንባብ ተሞክሮ ለማግኘት እና የቅርብ ጊዜ ዜናዎችን ለማየት መተግበሪያውን ያውርዱ።!

Download
Cancel
Image:AddisZena
አዲስ ዜና | Addis Zena
የሲዳማና የጋምቤላ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድሮቻቸውን መረጡ

የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌንዳሞና የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ

በኢትዮጵያ 10ኛ ክልል የሆነው የሲዳማ ክልል የክልሉን መንግሥት ለመመስረት የመጀመሪያ ጉባኤውን እያካሄደ ነው።

ስድስተኛውን ብሔራዊ ምርጫ ተከትሎ እያደረገ ባለው የመመስረቻ ጉባኤም አቶ ደስታ ሌንዳሞን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሾሟል።

በመካሄድ ላይ ባለው የክልል ምክር ቤቱ ጉባኤም ፋንታዬ ከበደን የመጀመሪያ አፈ ጉባኤ እንዲሁም አቶ ዘነበ ዘርፉን ምክትል አፈ ጉባኤ አድርጎ መርጧል።

በተያያዘ ዜና የጋምቤላ ክልል ምክር ቤትም የክልሉን መንግሥት ለመመስረት ጉባኤ እያካሄደ የሚገኝ ሲሆን አቶ ኡሞድ ኡጁሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሾሟል።

ከዚህ በተጨማሪም ወ/ሮ ባንቺ አየሁ ዲንገታን ዋና አፈ ጉባኤ እንዲሁም ወ/ሮ ትሁት ሃዋሪያትን ደግሞ ምክትል አፈ ጉባኤ አድርጎ ሾሟል።

አዳዲሶቹ አመራሮች በተሰጣቸው ኃላፊነትም ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።

የሲዳማና የጋምቤላ ክልል በመስራች ጉባዔያቸው በቀጣይ የሚያገለግሉ የካቢኔ አባላትና ሌሎች ሹመቶችን ያፀድቃሉ።

ከሁለት አመት በፊት ከሁለት ሚሊዮን ህዝብ በላይ መራጮች በላይ በተሳተፉበት ህዝበ ውሳኔ ከ98.5 በመቶ በላይ ክልል እንዲሆን መምረጡን ተከትሎ ሲዳማ 10ኛ የኢትዮጵያ ክልል መሆኗ ይታወሳል።

logoBBC rc47 cc0
አሁን የናኙ
Copyright © All rights reserved | Marvellous LLC